Main Content Section

About Us

eHaHu.com ምንድን ነው?

eHaHu.com ፈጣን ፤ ግልፅ ፤ ውጤታማ እና በሞባይልም ሆነ በማንኛውም ነገር ለመጠቀም እንዲመች ተደርጎ የተሰራ ኢትዮጵያዊ እና ማበረሰብን እንዲያገናኝ እና ህዝብን እንዲያገለግል ታስቦ የተዘጋጀ ድረ-ገፅ ነው፡፡ eHaHu.com ሲሰራ መሰረት ያደረገው ግልፅ ፤ ፈጣን እና በቀላሉ የሚለመድ እንዲሆን ሆኖ ነው፡፡ eHaHu.com ለፊልም እና ሲኒማ ቤቶች ፤ ለሁሉንም አይነት ዝግጅቶች ፤ ለእውቂያዎች ማስቀመጫ ፤ የየቀኑን የአየር ሁኔታን ጭምር የያዘ የኢትዮጵያውያን የመገበያያ ስፍራ ሲሆን ፤ ሁሉንም በአንድ ላይ እና በቀላሉ አዋህዶ የያዘ ድረ-ገፅ ነው፡፡

ፊልም እና ሲኒማ

ፊልምን ለሲኒማ እንደበቃ ቀድመው ማየት ይፈልጋሉ? አዎ ከሆነ መልስዎ፤ የ ፊልም እና ሲኒማ ገፃችን በከተማችን የሚገኙትን ዋና ዋና ሲኒማ ቤቶች መገኛ አድራሻ እና ፊልሞች ከነ ሙሉ ማብራሪያቸው ፤ የፊልም ቅንጫቢዎች (Trailers) ፤ የፊልሞችን ፖስተር ፤ የቀኑን ፤ የሳምንቱን ማሳያ(መታያ) ሰዓታቸውን እና በቅርብ ጊዜ የሚወጡትን ፊልሞች ፤ እንዲሁም በፊልሞች ላይ የተሰጠ ደረጃ እና አስተያየት የያዘ ሲሆን ፤ ቲ ሲኒማ ፤ አለም ሲኒማ ፤ እምቢልታ ፤ አጎና ፤ ሀድሜስ ፤ ሴባስቶፖል ፤ ካፍደም እና ሌሎችም ብዙዎቹ በአንዱና በብቸኛውeHaHu.com ከትመው ወቅታዊ እና ትክክለኛ የፊልም ማሳያ ሰዓታቸውን እያወጡ ይገኛሉ፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ 12 ሲኒማ ቤቶች እና ከ 2005 ዓ/ም ጀምሮ ለእይታ የበቁ ፊልሞች ከነ ሙሉ ማብራሪያቸው ሲፈልጉ በ አማርኛ አልያም በእንግሊዝኛ ቁልጭ ብለው ይገኛሉ:: በተጨማሪ

መግዣ እና መሸጫ

ምን መግዛት ይፈልጋሉ? አይፎን ፤ ጌጣጌጥ ፤ ወይስ የመማርያ መፀሐፍት? መኪና መከራየት ወይስ መሸጥ ይፈልጋሉ? የአዱ ገነት ነዋሪ ነዎት ወይስ የድሬ ፤ የትግራይ ወይስ የሐዋሳ? eHaHu.com ላይ ከሆኑ ያሉት ፤ መግዣ እና መሸጫ ክፍላችን ገዢና ሻጭን በሚገዙት ፤ በሚሸጡት ፤ ወይም ሊገዙ ባሰቡት አልያም ሊሸጡ በሚፈልጉት ነገር ላይ እንዲሁም በሚገኙበት ቦታ ሳይወሰን ያለከፍያ ለድርድር ያገናኛል፡፡ ኤሌክትሮኒክስ ፤ አልባሳት ፤ ተሸከርካሪዎች ፤ የቤት እና የቢሮ እቃዎች ፤ መኖርያ ቤቶች ፤ መፀሐፍት ፤ እና ሌላ ማንኛውንም ነገር በ eHaHu.com ላይ ይገኛል ፡፡ ላይ ይገኛል ፡፡ ቆይታዎን ቀላል እና የሚፈልጉትን ነገር በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ ለማድረግ የመሸጫ እና መግዣ ክፍላችን 8 ክፍሎች እና ከ 100 በላይ ንዑስ ክፍሎች እንዲኖሩት ያደረግን ሲሆን ይህም ማንኛውንም ነገር ለማካተት እና ለመግዛት የሚፈልጉትን ነገር በቀላሉ እንዲያገኙ ይረዳዎታል፡፡ eHaHu.com አዲስ ኢትዮጵያዊ የየቀን ስራዎን በምቾት እና በከፍተኛ ደረጃ እዲሰሩ ከማመቻቸቱም በላይ የሽያጭ ማስታቂያዎን እጅግ በጣም በቀላሉ እና በነፃ የሚያወጡበት ድረ-ገፅ ነው፡፡ በተጨማሪ

ዝግጅት

ዝግጅት ለማዘጋጀት እና ተጋባጅ እንግዶዎቾን ለመጥራት እያሰቡ ነው? ከሆነ ፤በ eHaHu ድረ-ገጽ የ “ዝግጅት”(Events) ክፍል ይህንን ጉዳይ ከመቼውም ጊዜ በላይ ቀላል ለማድረግ አስበን አዘጋጅተነው ተሳክቶልና፡፡ የእርስዎን ዝግጅት ለማተዋወቅም ሆነ በአቅራቢያዎ ያሉትን የተለያ ዝግጅቶች ማግኘት ቀላል ሆኗል፡፡ ዝግጅትዎን ለተመረጡ ተመልካቾች ወይም ለሁሉም ተመልካች በቀላሉ እና በነፃ ማውጣት ይቻላሉ በተጨማሪ

እውቂያዎች

የእጅ ስልክዎን ጥለው ያውቃሉ? በዚህ ጊዜ በስልካችን ላይ መዝግበን የያዝናቸውን አድራሻዎች እንደምናጣ እና ይህም እንዴት እንደሚያበሳጨን ይታወቃል፡፡ የ eHaHu.com “እውቂያዎች” ገፅ የስልክዎን እውቂያዎች በሙሉ በቀላሉ ይዞ በማስቀመጥ በማንኛውም ቦታ እና ስልክም ሆነ ኮምፒውተር ላይ ሆነው ማግኘት እንዲችሉ ያደርጋል፡፡ ይህ ክፍል የቤተሰብዎን ወይም ማንኛውንም አይነት የተመዘገበ አድራሻ በፍፁም እንዳይጠፋ አድርጎ እንዲያስቀምጥ በጥንቃቄ የተዘጋጀ ነው፡፡ የእርስዎ እውቂያዎች በሙሉ በጥንቃቄ ሚስጥራዊነቱ እንደተጠበቀ በ eHaHu.com መረጃ ቋት ላይ ይቀመጣል፡፡ አንድ ጊዜ ስልክዎ ላይ የሉት እውቂያዎች ወደ eHaHu.com ከተላለፉ ከ ገፁ ላይ ቀጥታ መደወል ይችላሉ፡፡ እንዲሁም የሚፈልጉትን ሰው አድራሻ በቀላሉ ፈልጎ ማግኘት ፤ ሁሉንም እውቂያዎች ወደ ኤክሴል (excel ) መውሰድ ፤ እንዲሁም ከቤተሰብዎ ጋር እና ከጕደኛዎ ጋር እንዲካፈሉ ያስችላል ፤ በተጨማሪ

የኔ ስፍራ

ይህ ቦታ ሁሉም የእርስዎ መረጃዎች የሚገኙበት ቦታ ነው፡፡ አንድ ጊዜ እዚህ ቦታ ከተገኙ ፤ የለጠፉትን ነገር ማስተካከልም ሆነ ማጥፋት ፤ አዲስ መለጠፍም ሆነ ሰዎች እንዳያዩት መሰወር ወይም ሌላ የፈለጉትን ማድረግ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪ

በቅርቡ የሚጀመሩ ገፆች

የስራ ገፃችን ላይ (ቀጣሪን እና ተቀጣሪን እናገናኛለን) ፤ የስፖርት ገፅ ፤ ወቅታዊ የሙዚቃ እና ተመሳሳይ ዝግጅቶች ፤ እና ሌሎችም ተመሳሳይ ገፆችን ለመክፈት ሌት ተቀን እየሰራን ሲሆን በስራ ላይ በዋሉት ገፆቻችንም ላይ በየቀኑ መሻሻልን ለማምጣት ቃላችንን ጠብቀን እየሰራን እንገኛለን በዚህም ዝናችን በኢትዮጵያ ውስጥ በቀላሉ እየተስፋፋ ይገኛል፡፡

Movie Listing Features

 • በአማርኛ እና በ እንግሊዘኛ ቋንቋ ይሰራል
 • በ ሞባይልም ሆነ በ ታብሌት ለመጠቀም እንዲመች ተደርጎ ተዘጋጅቷል
 • በወቅቱ የሚታዩትን ፊልሞች ዝርዝር ከነ አስተያት እና ደረጃቸው
 • የ ሲኒማ ቤቶች የ እለት እና የ ሳንትምንት ፊልም ማሳያ ፕሮግራም (በሲኒማ ቤቶቹ የሚስተካከል)
 • ፈጣን የፊልም መፈለጊያ
 • በቅርብ ጊዜ የሚወጡ ፊልሞች
 • የፊልሙን ተዋንያን እና ከመጋረጃ ጀርባ ያለውን መረጃ ዝርዝር
 • የፊልሙ አጭር መግለጫ
 • የፊልም ቅንጫቢ (Trailers)
 • የሲኒማ ቤቶች መገኛ አመላካች እና ስልክ ቁጥሮች
 • የተመልካች አስተያየት እና ደረጃ
 • የእርሶንም አስተያየት ማስገባትም እንዲችሉ ተደርጎ ተዘጋጅቷል

Buy & Sell Features

 • በአማርኛ እና በ እንግሊዘኛ ቋንቋ ይሰራል
 • በ ሞባይልም ሆነ በ ታብሌት ለመጠቀም እንዲመች ተደርጎ ተዘጋጅቷል
 • የሚሸጡ እቃዎች በጥሩ ሁኔታ በክፍል እና በንዑስ ክፍል የተቀመጡ ናቸው
 • ቁርጥ ዋጋ ያላቸውም ሆነ ለድርድር ክፍት የሆኑ እቃዎችን ለማውጣት ያስችላል
 • እቃው የተለጠፈበትን ቀን ያወጣል
 • ፈጣን መፈለጊያ (በቅርብ ጊዜ)
 • የለጠፍነውን ማስታወቂያ የጎበኙ ሰዎች ብዛት ያሳያል
 • ለአንድ እቃ እስከ 5 ፎቶዎች ማስገባ ያስችላል
 • ተመሳሳይ እቃዎችን በዋጋቸው ለይቶ ማውጣት ያስችላል (በቅርብ ጊዜ)
 • የሻጭ መገኛ አድራሻን ያሳያል
 • በተመሳሳይ ግለሰብ ወይም አካል የወጡ ሌላ እቃዎችን ያሳያል
 • የተመሳሳይ እቃዎች ዝርዝር
 • በየትኛውም ሰዓት እና ጊዜ የለጠፉትን እቃ ና ዋጋ ማስተካከልም ሆነ ማጥፋት ይችላሉ
 • እቃዎን ለመሸጥ በ ድረ-ገፅ ላይ ማውጣት እንዲህ ቀላ ሆኖ አያውቅምe

Events Features

 • በ ሞባይልም ሆነ በ ታብሌት ለመጠቀም እንዲመች ተደርጎ ተዘጋጅቷል
 • ዝግጅቶቹ በጥሩ ሁኔታ በክፍል እና በንዑስ ክፍል የተቀመጡ ናቸው
 • የዝግጅቶቹ ዝርዝር መረጃ ማለትም ቦታ ፤ ቀን እና ሰዓት ፤ የመግቢያ ዋጋ እና ሌሎችም ተካተው ይገኛሉ
 • ጎብኚው እንደሚገኝ በቀላሉ ማሳወቅ ሲችል ፤ አዘጋጁም ማን እንደሚገኝ እንዲሁ በቀላሉ ድረ-ገፃችን ላይ ማግኘት ይችላል
 • ፈጣን መፈለጊያ (በቅርብ ጊዜ)
 • የእርስዎ ዝግጅት ለዝግጅት አቀናባሪዎች ክፍት መሆኑን እና አለመሆኑን ያሳውቅዎታል
 • ለ ዝግጅቱ የተሰራውን ባነር እንዲለጥፉ የስችልዎታል
 • የዝግጅቱን ባለቤቶች መገኛ አድራሻ አብሮ ያወጣል
 • ተመሳሳይ ዝግጅቶችን ወይም በተመሳሳይ ቀን ያሉ ሌሎች ዝግጅቶችን ማግኘት እንድንችል ያስችለናል
 • ዝግጅትዎን ለተመረጡ ተመልካቾች ወይም ለሁሉም ተመልካች በቀላሉ ማውጣት ይቻላሉ
 • የርስዎን ዝግጅት በየትኛውም ጊዜ ማጥፋም ሆነ ማስተካከል ይችላሉ

Contacts Features

 • በ ሞባይልም ሆነ በ ታብሌት ለመጠቀም እንዲመች ተደርጎ ተዘጋጅቷል
 • ፈጣን መፈለጊያ
 • በቅደም ተከተል ማስተካከል እና ፤ በቤተሰብ ፤ በጕደኛ እና በመሳሰሉት ለይቶ ማውጣት ያስችላል
 • ከ እጅ ሰልክዎ ላይ ሆነው ከሆነ እውቂያዎቾን የሚጎበኙት ፤ ከዛው ላይ በቀጥታ መደወል ይችላሉ
 • እውቂያዎቾን ሁሉ ወደ ኤክሴል (excel ) በቀላሉ መውሰድ ይችላሉ

My Hub Features

 • በ ሞባይልም ሆነ በ ታብሌት ለመጠቀም እንዲመች ተደርጎ ተዘጋጅቷል
 • የእርሶን መረጃ ማስተካከል
 • የለጠፉትን ነገር ማተካከል ፤ ማጥፋት ፤ መሰወር እና ሌሎችም